Empowering Caregivers in Durame City Through Income-Generating Activities

Empowering Caregivers in Durame City Through Income-Generating Activities

The Parkinson Patient Support Organization Ethiopia is committed to integrating caregivers into income-generating activities, allowing them to improve their livelihoods while staying close to the patients they care for.
Caregivers who undergo training receive support based on their individual business proposals. Recently, Mrs Martha Hesebo, a caregiver trained in Durame City, was provided with support to start a business focused on baking and distributing Injera, traditional Ethiopian food.
Previously, Mrs. Hesebo traveled to various households to make a living by preparing Injera, which was challenging due to her husband’s Parkinson’s disease. With the new support, she can now bake Injera from home, minimizing travel requirements. Additionally, this support will allow her to send her child back to school, who had previously left due to his caregiving responsibilities.

****************************************************

ፓርኪንሰን ፔሸንት ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ በትኩረት ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ የሆነው አስታማሚዎችን በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ ማሰማራት አንዱ ሲሆን አስታማሚዎች ከህሙማኑ ሳይርቁ በገቢ ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት ኑሯቸውን የሚደጉሙበት ነው፡፡

አስታማሚዎች ስልጠና ከተሰጣቸው በሃላ በሚያቀርቡት የስራ ሃሳብ መነሻነት ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚህም በቅርቡ በዱራሜ ከተማ ስልጠና ከወሰዱ አስታማሚዎች መካከል አንዱ የሆነችው ማርታ ሄሴቦ ባቀረበችው እንጀራ ጋግሮ ለገበያ የማቅረብ ሃሳብ መሰረት ስራ ማስጀመሪያ የሚሆን ድጋፍ ተደርጎላታል፡፡

ከዚህ ቀደም ወይዘሮ ማርታ ወደተለያዩ ግለሰቦች ቤት በመሄድ እንጅራ በመጋገር ኑሮዋን የምትማራ ሲሆን ይህም ስራ የፓርኪንሰን ታማሚ ባለቤቷን ለማስታመም አመቺ ባለመሆኑ የ ሶስተኛ ክፍል ተማሪ ልጇን ከትምህርት ቤት በማስቀረት የባለቤቷ አስታማሚ ለማድረግ ተገዳ ነበር፡፡

ይህ ድጋፍ በተለያዩ ግለሰቦች ቤት በመሄድ ትሰራው የነበረውን የእንጀራ መጋገር ስራ በቤቷ ሆና መስራት የሚያስችላት ሲሆን ከትምህርት ገበታው የቀረው ልጇም ወደ ትምህርት ቤት የሚመልስ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

 

Add a Comment

Your email address will not be published.