Facing Darkness: The Struggles of Parkinson’s Patients in Rural Area

Facing Darkness: The Struggles of Parkinson’s Patients in Rural Area

During our trip to Kemebata Tembaro Zone, Durame City, the colleagues of the Parkinson’s Patient Support Organization Ethiopia had the opportunity to meet with numerous Parkinson’s patients. They encountered several significant challenges: the absence of a single neurologist in the area, issues with drug supply and pricing, the lack of a physiotherapy center, and poor road infrastructure, all of which have severely impacted the lives of these patients.

The situation is particularly dire for those living in rural areas. Parkinson’s disease, which impairs movement, exacerbates their difficulties, making their conditions even more complicated. Among the patients we met, Mrs. Tagesech Isaias exemplifies these struggles. Raising eight children as a single mother, she has lived in a dark room for the past ten years due to Parkinson’s disease. Due to mobility issues, she was unable to stand or attend her son’s funeral, which occurred a year ago. She became emotional when discussing this loss.

A recent leg wound, compounded by her Parkinson’s, has further complicated Mrs. Tageseh’s life. Economic constraints and mobility issues, combined with poor road infrastructure, have prevented her from receiving proper treatment. We observed that the road leading to her residence is not suitable for bajaj or motorcycles, which further hinders her ability to access medical care.

As a result, Mrs. Tageseh remains confined to a dark room, facing an increasingly difficult future due to the untreated wound and ongoing lack of medical support. Beyond the stigma associated with Parkinson’s disease, patients like Mrs. Tageseh in rural areas face numerous challenges: inadequate treatment options, poor road infrastructure, economic hardships, and issues with drug supply.

Currently, the only organization in our country dedicated to Parkinson’s disease, PPSOE, is struggling to reach these patients due to limited resources. However, addressing these challenges remains a critical priority for the organization’s future initiatives.

****************************************************************************************************

ጨለማን የተጋፈጡ የፓርኪንሰን ህሙማን!

 

የፓርኪንሰን ፔሸንት ሰፓርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ ባልደረባዎች ወደ ከምባታ ጠንባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ በተጓዝንበት ወቅት ከበርካታ የፓርኪንሰን ህሙማን ጋር የመገናኘት አጋጣሚውን አግኝተን ነበር፡፡ በተለይም በአካባቢው አንድም የነርቭ ሀኪም አለመኖሩ፤ የመድሃኒት አቅርቦትና ዋጋ ንረት ችግር፤ የፊዚዮቴራፒ ማዕከል አለመኖር እንዲሁም የመንገድ መሰረተ ልማት ችግር የታማሚዎችን ህይወት እጅግ አክብዶታል፡፡

በተለይም አብዛኞቹ ህሙማን በገጠራማው አካባቢ እንደመኖራቸው እንቅስቃሴ ከሚገድበው የፓርኪንሰን ህመም ጋር ተዳምሮ ሁኔታቸውን እጅግ አወሳስቦታል፡፡

በጉዟችን ወቅት ካጋጠሙን ህሙማን መካከል ወይዘሮ ታገሰች ኢሳያስ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ናቸው፡፡ 8 ልጆችን ያለአባት በማሳደግ የህይወት ውጣ ውረድ ሂደት ውስጥ የፓርኪንሰን ህመም ያጋጠማቸው ወይዘሮዋ ለለፉት አስር አመታት በአንዲት የጨለማ ክፍል ውስጥ ህይወታቸውን በመግፍት ላይ ናቸው፡፡ በተለይም ከአንድ አመት በፊት በሞት ያጡትን ልጃቸውን ቆመው መቅበር አልቻሉም፡፡ ስለዚህ አጋጣሚ ሲናገሩ እምባ እየተናነቃቸው ነበር፡፡

ከቅርብ ጊዜ በኃላ ያጋጠማቸው የእግር መቁሰል ህመም ከፓርኪንሰን ህመም ጋር ተዳምሮ የህይወታቸውን ፈተና አክብዶባቸዋል፡፡ ካለባቸ የኢኮኖሚ፤ የእንቅስቃሴ ችግር እንዲሁም በአካባቢው ካለው የመንገድ መሰረተ ልማት አንጻር ህክምና ማግኘት አልቻሉም፡፡ በስፍራው ተገኝተን ለመታዘብ እንደቻልነው የወይዘሮ ታገሰች መኖሪያ ቤት ባጃጅም ሆነ ሞተር ሳይክል የሚያስገባ አይደለም፡፡

በዚህም ሳቢያ ወይዘሮ ታገሰች በአንዲት የጨለማ ክፍል ውስጥ ተኮራምተው ይገኛሉ፡፡ በተለይም በእግራቸው ላይ ያለው ቁስል ህክምና ሳያገኝ ከመቆየቱ ጋር ተዳምሮ መጪውን ጊዜ ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል፡፡ በየገጠሩ የወይዘሮ ታገሰች መሰል የፓርኪንሰን ህሙማን ከህመሙ ጋር ተያይዞ ከሚደርስባቸው መገለል ባሻገር የህክምና እጦት፤ የመንገድ መሰረተ ልማት ችግር፤ የኢኮኖሚ ችግር፤ የማስታገሻ መድሃኒት አቅርቦት ችግር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ጋር ተደማምረው ፈተናቸው በርካታ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ብቸኛው በፓርኪንሰን ህመም ዙሪያ የሚሰራው ድርጅታችን ፓፔሰኦኢ በአቅም ማነስ ለእነዚህ ህሙማን መድረስ ያልቻለ ሲሆን በቀጣይ ግን ከያዛቸው ውጥኖች መካከል ዋነኛው ለእነዚህ ህሙማን መድረስ ነው፡፡

 

Add a Comment

Your email address will not be published.