Capacity Building Workshop Held in Asella Town

Capacity Building Workshop Held in Asella Town

On December 17 and 18, 2024, Parkinson Patients Support Organization (PSO-E) organized a capacity-building training workshop for General Practitioners at Asella Referral and Teaching Hospital, collaborating with the Hospital’s Continuous Professional Development (CPD) Center.

The workshop focused on Parkinson’s Disease Diagnosis and Management, with neurologist Dr. Desalegn Yaye leading the training. A total of 20 General Practitioners participated and were certified upon completion. This training is part of PPSOE’s broader capacity-building initiatives.

Given the limited number of neurologists and the shortage of specialists in the area, such training is crucial for improving the accuracy of Parkinson’s disease diagnoses.

In her closing remarks, Mrs. Sofia, a representative from the Ministry of Health, acknowledged the importance of the training and emphasized the need for similar initiatives to be expanded to other regions. She also reaffirmed the Ministry’s commitment to cooperating with the mission of PPSOE, delivering her remarks virtually.

የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ታህሳስ 9 እና 10 ቀን 2017 አ.ም ፓርኪንሰንስ ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ ከአሰላ ሪፈራል እና ማስተማሪያ ሆስፒታል ተከታታይ የሙያ ልማት (CPD) ማእከል ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

በነርቭ ሐኪሙ ዶክተር ደሳለኝ ያየ የተሰጠው ስልጠና በፓርኪንሰን በሽታ ምርመራ እና ህክምና ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በሆስፒታሉ የሚገኙ ዶክተሮች እንዲሁም በከተማው ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የተውጣጡ 20 አጠቃላይ ሀኪሞች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን በአግባቡ በማጠናቀቃቸውም የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህ ስልጠና የፓርኪንሰንስ ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ የአቅም ግንባታ ስራ አካል ነው።በሀገራችን ብሎም በአካባቢው ካለው ከፍተኛ የነርቭ ሐኪሞች እጥረት አንጻር ይህ ስልጠና የፓርኪንሰን ህሙማን ተገቢውን ምርመራና ህክምና እንዲያገኙ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ ወይዘሮ ሶፊያ ሰኢድ በበይነ መረብ ባካሄዱት የመዝጊያ ንግግር የስልጠናውን አስፈላጊነት አጽንዎት በመስጠት መሰል ተግባራት ወደ ሌሎች ክልሎችም መስፋፋት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። በተጨማሪም የፓርኪንሰንስ በሽታን በተመለከተ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በቅንጅት መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፓርኪንሰንስ ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህ ቀደም መሰል ስልጠና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ጠንባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ በሚገኘው የዶክተር ቦጋለች ገብሬ ሆስፒታል መስጠቱ  ይታወቃል፡፡

Add a Comment

Your email address will not be published.