የአስታማሚዎች ስልጠናና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር

የአስታማሚዎች ስልጠናና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር

የአስታማሚዎች ስልጠናና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር #በፓርኪንሰን_ፔሸንትስ_ሳፖርት_ኦርጋናይዜሽን_ኢትዮጵያ
#የፓርኪንሰን ህሙማን አስታማሚዎችና ተንከባካቢዎች በማስታመሙ ሂደት ምን ሊያጋጥማቸው ይችላል በሚል የተዘጋጀው ስልጠና ተካሂዷል።
በዋናነት ስልጠናው ትኩረቱን ያደረገው የፓርኪንሰን ህሙማንን የሚያስታምሙና የሚንከባከቡ የቤተሰብ አባላት ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባር እንዲሁም ስለበሽታው ባህሪ ግንዛቤ መፈጠር ላይ ነው።
ከፓርኪንሰን በሽታ ባህሪ አንፃር አስታማሚዎችና ተንከባካቢዎች ስለበሽታው ባህሪ በቂ መረጃ ሊኖራቸው ይገባል ያሉት የስልጠናው አስተባባሪ ወይዘሮ የአብስራ ዘላለም አስታማሚዎች በማስታመሙ ሂደት የራሳቸውንም ሂወት ሳይዘነጉ ከሌሎች የቤተሰብ አባላት እገዛ እየጠየቁ ካልሆነ የሚደርስባቸው የስነልቦና ጫና ከባድ ይሆናል ብለዋል።
የስልጠና ተሳታፊ የሆኑ አስታማሚዎች በበኩላቸው የሚያጋጥማቸውን ችግር በስፋት በማንሳት የተለያየ ተሞክሯቸውን አጋርተዋል።
በተጨማሪም አስታማሚዎቹ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፥ የስነልቦና፥ ማህበራዊና አካላዊ ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነም አንስተዋል። በታማሚው ከመመታት እስከ ትዳር መፍረስ የመሳሰሉት ጫናዎችን ተቋቁመው በማስታመም ላይ ይገኛሉ።
May be an image of 8 people and people studying  May be an image of 8 people

Add a Comment

Your email address will not be published.