Primary Healthcare Guideline for Neurological Conditions Officially Launched: A Major Milestone for People Living with Parkinson’s Disease in Ethiopia

Primary Healthcare Guideline for Neurological Conditions Officially Launched: A Major Milestone for People Living with Parkinson’s Disease in Ethiopia

Primary Healthcare Guideline for Neurological Conditions Officially Launched: A Major Milestone for People Living with Parkinson’s Disease in Ethiopia

We are thrilled to announce the official launch of the Primary Healthcare Guideline, a significant milestone that PPSOE has long advocated for.

On Friday, November 20, 2026, the guideline was officially launched by the Association of Ethiopian Neurologists and the Ministry of Health, in collaboration with national and international partners.

This guideline will help ensure that people living with Parkinson’s disease can receive care and treatment at the primary healthcare level, bringing essential medical services closer to their communities.

PPSOE played a key role throughout this process, from preparing and advocating for the policy brief to supporting the initiative through its final stages.

With the launch of this guideline, we look forward to a future in which people living with Parkinson’s disease can access essential medical services at nearby primary healthcare centers.

We extend our heartfelt gratitude to the Ministry of Health, the Association of Ethiopian Neurologists, and all national and international partners who contributed to making this important achievement possible.

This is an important step forward in improving access to healthcare for people living with Parkinson’s disease in Ethiopia.

**********************************************************

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የነርቭ ህመሞች ሕክምና መመሪያ ይፋ ሆነ፤ ከፓርኪንሰንስ በሽታ ጋር ለሚኖሩ ወገኖች ታላቅ ምዕራፍ

ድርጅታችን (PPSOE) ለረጅም ጊዜ በትኩረት ሲሠራበት የቆየው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የነርቭ ሕክምና መመሪያ ይፋ መሆኑን ስንገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማናል።

ዓርብ ኅዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ የነርቭ ሐኪሞች ማኅበር እና በጤና ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ይፋ ተደርጓል።

ይህ መመሪያ ከፓርኪንሰንስ በሽታ ጋር የሚኖሩ ወገኖች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት (ጤና ጣቢያዎች) የሕክምና እና የክብካቤ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ መሠረታዊ የሕክምና አገልግሎቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ይበልጥ ያቀርባል።

ድርጅታችን የፖሊሲ ሃሳቡን ከማዘጋጀትና ፖሊሲ አውጪዎችን ከማግባባት አንስቶ፣ እስከ መጨረሻው ምዕራፍ ድረስ ሂደቱን በመደገፍ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።

በዚህ መመሪያ መመረቅ ምክንያት፣ ከፓርኪንሰንስ በሽታ ጋር የሚኖሩ ወገኖች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የጤና ጣቢያዎች መሠረታዊ የሕክምና አገልግሎቶችን የሚያገኙበት ብሩህ ተስፋ ይታየናል።

ይህ ታላቅ ስኬት እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ የነርቭ ሐኪሞች ማኅበር እንዲሁም ለሁሉም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ አጋር አካላት ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ከፓርኪንሰንስ በሽታ ጋር የሚኖሩ ወገኖችን የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሻሻል የተወሰደ ትልቅ የለውጥ እርምጃ ነው።

 

Add a Comment

Your email address will not be published.