PPSOE’s Visit to Durame Town and Surrounding Areas

PPSOE’s Visit to Durame Town and Surrounding Areas

For six years, PPSOE has supported Parkinson’s patients and their families in Durame Town and nearby communities, in collaboration with Dr. Bogalech Gebre Memorial Hospital.

During a week-long visit, PPSOE staff:

  • Provided resources—including goats, sheep, hens, butter, flour and pans —to caregivers who had received training earlier to start small businesses
  • Distributed medicines and sanitary materials to 50 patients

Most caregivers in the area are farmers. These initiatives help them improve livelihoods while continuing patients care.

PPSOE will continue these efforts until all caregivers in need have been reached, reinforcing our ongoing mission to provide both medical and socio economic support.

የፓፔሰኦኢ ድጋፍ በዱራሜ ከተማና አካባቢው

ላለፉት ስድስት አመታት ፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ ከዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በዱራሜ ከተማና አካባቢዋ ለሚገኙ የፓርኪንሰን ህሙማንን  ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል። 

ባለፈው አንድ ሳምንት የፓፔሰኦኢ ሰራተኞች በስፍራው በመገኘት በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል። ከእነዚም መሀል፤

  • ከዚህም ቀደም ስልጠናቸውን አጠናቀው ስራ ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ አስታማሚዎች ባቀረቡት ሀሳብ መሰረት ፍየል፤ በግ፤ ዶሮ፤ ቅቤ፤ የጤፍ ዱቄት እና ምጣድ በመግዛት አስረክበዋል።
  • ለ50 ህሙማን ለአንድ ወር የሚሆናቸውን የመድሃኒትና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርገዋል።
  • አብዛኖቹ አስታማሚዎች በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ በመሆናቸው እንዲህ አይነቱ የእንስሳት እርባታ ስራ የህሙማኑን ቤተሰቦች በኢኮኖሚ ለመደገፍ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው።
  • ፓፔሰኦኢ  አስታማሚዎችን በኢኮኖሚ የማብቃቱን ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።


Add a Comment

Your email address will not be published.