Emmanuel Mental Specialized Hospital Provides Medicine Support
Emmanuel Mental Specialized Hospital has provided one month of medication support for 75 patients, in response to the ongoing shortage and rising costs of medicines for Parkinson’s disease.
This initiative is especially valuable as many patients have been struggling with severe hardships due to the recent shortage and price increases of Parkinson’s drugs.
On behalf of the patients, our organization extends heartfelt gratitude to the hospital management, staff, and Dr. Mikias — a hospital physician and dedicated volunteer of our organization — for coordinating this vital support.
********************************
አማኑኤል የአምዕሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመድሃኒት ድጋፍ አደረገ
ሆስፒታሉ የፓርኪንሰን ታማሚዎች ያጋጠማቸውን የመድሃኒት እጥረትና የዋጋ ውድነትን ከግምት በማስገባት ለ75 ህሙማን ለአንድ ወር የሚሆናቸውን መድሃኒት ድጋፍ አድርጓል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የፓርኪንሰን መድሃኒት እጥረትና ዋጋ ንረት ምክንያት ህሙማኑ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ከመሆናቸው አንጻር ይህ ድጋፍ ያለው ፍይዳ ከፍተኛ ነው።
ድርጅታችን በህሙማኑ ስም ለሆስፒታሉ አመራሮች፤ ሰራተኞች እንዲሁም ይህ ድጋፍ እንዲደረግ ያስተባበረውን የድርጅታችን በጎ ፍቃደኛና የሆስፒታሉ ሰራተኛ ዶክተር ሚኪያስን ከልብ ያመሰግናል።






