በፓርኪን ህመም ልየታና ህክምና የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በፓርኪን ህመም ልየታና ህክምና የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በፓርኪንሰን ፔሸንት ሰፓርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያና የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ የሞያ ማልበቻ ማዕከል በጋራ ያዘጋጁት በፓርኪንሰን ህመም ልየታና ህክምና በተመለከተ የአሰልጣኞች ስልጠና በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል ለሚገኙ ዶክተሮ ች ተሰጥቷል ፡፡ ስልጠናው በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በነርቭ ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ዘለቀ ወልደ ዮሀንስ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በዱራሜ ከተማና አካባቢው የሚገኙ የፓርኪንሰን ህሙማን የተሻለ የህክምናና የህመምል የታእንዲያገኙ ያስችላል፡፡ በዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል የሚገኙ 35 የህክምና ዶክተሮች ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን በቀጣይ በአካባቢው ለሚገኙ ህሙማን የተሻለ የህመምል የታናህክምና እንዲሰጡ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ የዶክተር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ደርበው ስልጠናውን ላዛጋጁት ፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያና የአዲስ አበባ ዩኒቭርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅን አመስግነው ስልጠናው የሆስፒታሉን ሀኪሞችን ክህሎትና አቅም በማሳደግ ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት አቅም በማሳደግ ደረጃ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ተወካይ የሆኑት ወይዘሮ ጸሀይ አየለ ስልጠናው በሀገራችን ካለው አነስተኛ የነርቭ ሀኪሞች ቁጥር አንጻር እንዲህ አይነቱ ስልጠና ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ እንዲ ያደርጉ በማሳሰብ በቀጣይ በክልሉ ላሉ የጤና ባለሞያዎች ለሚሰጠው ስልጠና በአሰልጣኝነት እንደሚያገለግሉ ያላቸውን ተስፋገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም በነርቭ ስፔሻሊስቱ ዶክተር ዘለቀ ወልደ ዮሀንስና ሰልጣኝ ሀኪሞች አማካኝነት በዱራሜ ከተማና አካባቢዋ ለሚገኙ የፓርኪንሰን ህሙማን ነጻ የህክምናና የምክር አግልግሎት ተሰጥቷቸዋል፡፡

Add a Comment

Your email address will not be published.