Support Group and Medication Assistance for Parkinson’s Disease in Durame Town
Support Group and Medication Assistance for Parkinson’s Disease in Durame Town
Last week, PPSOE conducted the final Parkinson’s disease support group session for 2025 in Durame Town. During the session, patients shared their experiences with one another, and caregivers also participated by sharing their experiences. In addition to experience sharing, PPSOE provided cash support to help patients purchase medication for one month.
The Durame support group is part of the TrAPCaf Project and Parkinson Africa. PPSOE extends its sincere gratitude to TrAPCaf and Parkinson Africa for their continued support.
በዱራሜ ከተማ ለፓርኪንሰን ሕመምተኞች የተደረገ የድጋፍ ቡድን ውይይት እና የመድኃኒት ድጋፍ
ፓርኪንሰንስ ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ የ2025 የመጨረሻ የሆነውን የፓርኪንሰን ህሙማን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በዱራሜ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ፦
- ሕመምተኞች እርስ በእርሳቸው የነበራቸውን ተሞክሮ ያካፈሉ ሲሆን፣ አስታማሚዎችም የማስታመም ሂደትን በተመለከተ የነበራቸውን ልምድ አጋርተዋል።
- ከልምድ ልውውጡ በተጨማሪም፣ ሕመምተኞች የአንድ ወር መድኃኒታቸውን መግዛት እንዲችሉ ድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ይህ የዱራሜው የህሙማን የልምድ ልውውጥ ቡድን የTrAPCaf እና የፓርኪንሰን አፍሪካ (Parkinson Africa) ፕሮጀክት አካል ነው። ድርጅታችን ለTrAPCaf እና ለፓርኪንሰን አፍሪካ ላላሰለሰ ድጋፋቸው ያለውን ጥልቅ ምስጋና ያቀርባል።







